1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ሪያል ማድሪድ ከባዬርን ሙይንሽን

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2016

በሻምፒዮንስ ሊግ የደርሶ መልስ የግማሽ ፍጻሜ ግጥሚያ ዛሬ ማታ የጀርመኑ ባዬርን ሙይንሽን ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ ጋ ይጋጠማል ። ባዬርን ሙይንሽን ዛሬ ማታ ማሸነፍ ከቻለ፦ ሁለቱ የጀርመን ቡድኖች ለፍጻሜ በመድረስ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2013 የነበራቸው ታሪክ ይደገማል ማለት ነው ።

https://p.dw.com/p/4fdy4
Halbfinale der Champions League | Dortmund - PSG
ምስል Matthias Schrader/AP/picture alliance

በሻምፒዮንስ ሊግ የደርሶ መልስ የግማሽ ፍጻሜ ግጥሚያ ዛሬ ማታ የጀርመኑ ባዬርን ሙይንሽን ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ  ጋ ይጋጠማል ። ትናንት በነበረው ጨዋታ ሌላኛው የጀርመን ቡድን ቦሩስያ ዶርትሙንድ የፈረንሣዩ ፓሪ ሳን ጃርሞን 1 ለ0 አሸንፏል ። በደርሶ መልስ የ2 ለ0 ውጤትቱም ቦሩስያ ዶርትሙንድ እንግሊዝ ዌብሌይ ስታዲየም ውስጥ ግንቦት 24 ለሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ማለፉን አረጋግጧል ። ባዬርን ሙይንሽን በሜዳው አሊያንትስ አሬና ስታዲየም ባደረገው ግጥሚያ የተለያየው በሁለት እኩል ውጤት ነበር ።

ዛሬ ማታ ሪያል ማድሪድን በሜዳው ሳንቲያጎ ቤርናቤዉ ይገጥማል ። ባዬርን ሙይንሽን ዛሬ ማታ ማሸነፍ ከቻለ፦ ሁለቱ የጀርመንቡድኖች ለፍጻሜ በመድረስ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2013 የነበራቸው ታሪክ ይደገማል ማለት ነው ። በወቅቱ በፍጻሜው ባዬርን ሙይንሽን ቦሩስያ ዶርትሙንድን በአሪዬን ሮበን የመጨረሻ ደቂቃ ግብ 2 ለ1 አሸንፎ ዋንጫ ወስዶ ነበር ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ-እግዚአብሔር