Negash Mohammedማክሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2016የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ኃይላት ከሱዳን ጦር ጋር ወግነው እየተዋጉ ነው በማለት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ያቀረበውን ክስ የትግራይ ክልል ዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ። በአማራ ክልል የሰሜን ጎጃም ዞን መምህራን ደመወዝ ከተከፈላቸው ከ2 ወራት በላይ መሆኑን ዐስታወቁ።የቅድመ ክስ እሥርን ለመቆጣጠር እና ለማስቀረት እንዲሁም የፍትሐዊ እና ሰብአዊ መብት መርኾችን ያካተተ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት፤ የፍትሕ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል