የተባበሩት መንግሥታት ጸጥታ ም/ቤት የሶሪያዉ ፕሪዝደንት ባሽር አልአሳድ የቀጠሉትን የጅምላ ጭፍጨፋ ለመግታት በሶርያ መንግስት ላይ የቀረበዉን የዉሳኔ ሃሳብ ሩስያ እና ቻይና ዳግም ማሰናከላቸዉ ተገለጸ።
በይግባኝ ባይ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤና በመልስ ሰጪ ተከሳሽ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማኅበራት ኤጀንሲ መሃል የተጀመረዉን ክርክር ዛሬ ለዉሳኔ የቀጠረዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዉን ለሌላ ቀን ቀጠረ።
18ኛዉን የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ካስተናገደችዉ ከመዲና አዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ የለቱ ትኩረት በአፍሪቃ ርዕስ ነዉ። በሁለት መቶ ይሮ ወጭ ታንጾ ከቻይና መንግስት ለህብረቱ የተበረከተዉ ግዙፍ ህንጻ ዉስጥ ለመጀመርያ ግዜ የተሰበሰቡት የአፍሪቃ ህብረት መሪዎች ተወያዩ?
የሶሪያውን ውዝግብ ሰላማዊ እልባት ማግኘት ባለመቻሉ፣ በፕርዚዳንት በሺር አል አሰድ አገዛዝ ላይ ተጨማሪ እርምጃ ይወሰድ ዘንድ የቀረበውን ረቂቅ ውሳኔ ፤ ሩሲያና ቻይና ድምጽን በደምፅ የመሻር መብታቸው፣ውድቅ ካደረጉት ወዲህ ፣ ጉዳዩ ብዙ በማነጋገር ላይ ነው።
ጀርመን ውስጥ በሙዩኒክ ከተማ የተካሄደው የ 3 ቀናት ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳይ ጉባዔ ፣ በዐበይትና ጥቃቅን ጉዳዮች ላይ በሰፊው ከመከረ በኋላ፣ ትናንት ማምሻውን ተደምድሟል።
ብዙሃኑ የአውሮፓ ሕብረት ዓባል መንግሥታት መሪዎች ብራስልስ ላይ ባካሄዱት ጉባዔ ከትናንት በስቲያ ጥብቅ የበጀት ቁጥጥርን በሚያሰፍን አንድ ውል ለመስማማት በቅተው ነበር።
በኢንዱስትሪ የገሠገሡት አገሮች፤ ለፋብሪካዎቻቸው ማሠሪያ የሚጠቀሙባቸው አንዳንድ የኃይል ምንጮች፤ ድንጋይ ከሰል ነዳጅ ዘይት፣
የነዳጅ ዋጋ መናር እና የምንጩ አስተማማኝነት ብቻ ሳይሆን፤ ከባቢ አየር ላይ የሚያስከትለዉ አሉታዊ ጫናም ጭምር ነዉ፤ የዓለምን
የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር ወደ ሩብ ፍጻሜው እየተሸጋገረ ነው። የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር ወደ ሩብ ፍጻሜው እየተሸጋገረ ሲሆን አስተናጋጆቹ ሃገራት ኤኩዋቶሪያ ጊኒና ጋቡን ጠንከር ባሉ ምድቦቻቸው ውስጥ ፉክክሩን በመቋቋም
ግሎባል አይዲያስ
ዶይቸ ቬለ በቴሌቪዥን፡ በራድዮ ወይም በኢንተርኔት የሚያቀርበውን ዝግጅት በአዲሱ የዴቬ አርማ ሥር ተጠቃሎዋል።
በአዲስ መንገድ የተዋቀረው አዲሱ የዶይቸ ቬለ ድረ ገፅ ሥራ ላይ ውሎዋል። ይህ በከፍተኛ የጋዜጠኝነት ሙያ የተዋቀሩትን ዝግጅቶች ለተጠቃሚዎቻችን በዘመናዩ መዋቅር ዝግጁ ያደርጋል።
ዴቬ አሁንም ከአልባንኛ እስከ ኡርዱ ቋንቋዎች፡ በሠላሳ ቋንቋዎች ዝግጅቶቹን ማቅረብ ቀጥሎዋል።
ፎቶዎች፡ ቪድዮዎች እና በጥልቀት የተዘጋጁ መረጃዎች በአዲሱ ድረ-ገፅ ተጨማሪ ቦታ አግኝተዋል።
አዲሱ ድረ-ገፅ የተለያዩትን የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን፡ ማለትም፡ ቪድዮዎችን፡ ድምፆችን፡ በኢንተርኔት የሚቀርቡ ዘገባዎችኝ የፎቶ ስብስቦችን እና ተጠቃሚዎች በቀጥታ የሚጠቀሙባቸውን አገልግሎቶችን ባንድነት አጠቃሎ የያዘ ነው።
የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል፡ የዴቬ የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎቶች ማከማቺያ በአዲሱ ድረ-ገፅ www.dw.de ተጠቃሎዋል። ተጠቃሚዎች በቀጥታ ሊገለገሉባቸው ይችላሉ።
ለምሳሌ «Destination Europe»ን የመሳሰሉ ልዩ ዝግጅቶች በአዲሱ ድረ-ገፅ ተካተዋል።
ወደ አውሮጳ ስለሚፈልሱ ወጣት አፍሪቃውያን በቪድዮ፡ በራድዮ ድራማ እና በኢንተርኔት የሰፈሩ ጽሑፎች የሚታዩበትና የሚነበቡበት ልዩ ፕሮጀክት ይቀርብበታል።
የራድዮው እና የቴሌቪዥኑ ዘርፎች በዴቬ ታሪክ ውስጥ አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ የጋራ የመክፈቻ ሙዚቃ አውጥተዋል።
ፌስቡክ፡ ትዊተር፡ እና መሰል የማህበራዊው መረብ አገልግሎቶች በአዲሱ የዶይቸ ቬለ ድረ-ገፅ ቦታ ይዘዋል። ዴቬ ከተጠቃሚዎችም ጋ በቀጥታ ለመገናኘት ዝግጁ ሆኖዋል።
የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ የሚከተለውን ማገናኛ ይጫኑ። አስተያየታችሁ ዓቢይ ግምት የሚሰጠው ነው፤ በamharic@dw.de ላኩልን፣ በ +49-228-429-164995 ደውሉልን። በዕለቱ ዓቢይ ርዕስ ላይ በ+49 172 26 66 944 SMS አስተያየት ላኩልን። 16:00 - 17:00 UTC የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆ በዚህ ሊንክ ይገኛል።
በማዳመጥ መማር የተባለው የዶቼ ቬለ አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን የርቀት ትምህርት በሁሉም የአህጉሪቱ ክፍሎች እውቀትን ለማዳረስ ይጥራል። »